04 Jul 2023
ሰኔ 3 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአባልነት ሲያገለገሉ የቆዩት አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ፣ ዶ/ር አብርሃም በላይ እና አቶ ነብዩ ሳሙኤል የአገልግሎት ዘመናቸውን አጠናቀው የክብር ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡ በዕለቱ ተሰናባች የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ለተኩት ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ፣ ወ/ሮ ትዕግስት ሀሚድ እና አቶ ወንድምአገኘው ነገራ እንዲሁ የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
04 Jul 2023
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዋናው መስሪያ ቤት በተዘጋጀ መርሀ ግብር የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ለበይክ ሙዳራባህ የተሰኘ አዲስ የሲቢኢ ኑር የቁጠባ ሒሳብ አገልግሎት ያስተዋወቀ ሲሆን፣ 3ኛውን ዙር "ሐጅ ለሁሉም" የንቅናቄ መርሃ ግብርም በይፋ አስጀምሯል።
04 Jul 2023
በኢትዮጵያ አስተማማኝ ዲጂታል የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝ በታለመው በዚህ የልምድ ልውውጥ ላይ በአቶ አቤ ሳኖ የሚመራ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ አመራር አባላት ልኡክ በመሳተፍ ላይ ይገኛል፡፡
04 Jul 2023
በሃገራችን ሁለንተናዊ የልማት እና የዕድገት ጉዞ ውስጥ ቀዳሚ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም በአጋርነት፤ ዜጎች ዲጂታል የብድር እና የቁጠባ አገልግሎቶችን በቴሌብር እንዲያገኙ የሚያስችል የሞባይል የፋይናንስ አገልግሎት ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀ መርሐ-ግብር በይፋ አስጀምረዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት በአጋርነት ያስጀመሩት አገልግሎት የባንክ እና የፋይናንስ አገልግሎትን ተደራሽነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋግጥ የሚያስችል፣ ዜጎች ባሉበት ሆነው ፈጣን እና ቀላል በሆነ አማራጭ የፋይናንስ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡