News Archive

19 Mar 2024

ባለፉት ስምንት ወራት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ከ10 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሪዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለፁት ባለፉት ስምንት ወራት በባንኩ ዲጂታል አገልግሎቶች በተከናወኑ ከ800 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች ከ10 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝውውር ተፈፅሟል፡፡ ይህም ከአጠቃላዩ የገንዘብ ዝውውር 73 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

19 Mar 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ ገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ ገለፀ፡፡ የደንበኞች የግል ሂሳብ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም፡፡

19 Mar 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት ተገለፀ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት ተገለፀ፡፡ • ባንኩ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ሥርዓት አለው ተብሏል፡፡

18 Nov 2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡

“ስኬታማ ምዕራፍ፤ ብሩህ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው የሲቢኢ ኑር 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል አንዱ አካል ሆኖ በተከታታይ የሚካሄደው የደንበኞች ምክክር መድረክ በዛሬው እለት (ህዳር 8፤ 2016) በአዲስ አበባ ከሚገኙ የሲቢኢ ኑር ደንበኞች ጋር በማካሄድ ተጀምሯል፡፡