30 Mar 2024
በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት ባንኩ መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ም ሌሊት በተፈጠረ ችግር ምክንያት አላግባብ ከተወሰደበት 801,417,747.81 ብር ውስጥ 622.9 ሚሊዮን ብር (78 በመቶ) እስካሁን የተመለሰ ሲሆን ብር 168,609,283.7 ለመመለስ ቃል ተገብቷል፡፡ አቶ አቤ አላግባብ በ567 ግለሰቦች የተወሰደውን ቀሪ ብር 9,838,329.12 ለማስመለሰ ባንኩ ወደቀጣይ እርምጃዎች እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
26 Mar 2024
ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 6፣ 2016 ዓ.ም ሌሊት በተፈጠረ ችግር ምክንያት 801,417,747.81 ብር ያላግባብ ተወስዶ እንደነበር ባንኩ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ያሳወቀ ሲሆን፣ 622.9 ሚሊዮን ብር ማስመለስ መቻሉ ተገልጿል፡፡ ከባንኩ አላግባብ የተወሰደውን ገንዘብ ለማስመለሰ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ በተዘጋጀው በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት ችግሩ በተከሰተበት ቀን ከምሽቱ 3፡38 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 8፡45 ድረስ በ25,761 ሂሳቦች አማካኝነት 238‚293 ህገወጥ ግብይቶች ተከናውነዋል፡፡
21 Mar 2024
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካጋጠመው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱና ያልተገባ የገንዘብ እንቅስቃሴ ካከናወኑ ግለሰቦች መካከል ብዙዎች የተደረገላቸውን ጥሪ ኣክብረው የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች እየቀረቡ እየመለሱ በመሆኑ ከስህተታቸው የመመለስ በጎ ምላሽነቱን እናደንቃለን። እስካሁን ቀርበው ገንዘቡን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦችም እስከመጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመቅረብ ተመላሽ እንዲያደርጉ ባንካችን የመጨረሻ ጥሪ ያቀርባል፡፡
19 Mar 2024
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት በጊዜያዊነት መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መግለጫ ***** መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የባንኩ መደበኛ አገልግሎቶች ለተወሰኑ ሰዓታት መቋረጣቸዉ ይታወቃል፡፡