News Archive

24 Jun 2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለ10 አመት የሚቆይ የ200 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረሙ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለ10 አመት የሚቆይ የ200 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረሙ፡፡ ========================= ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነቱን ለማሳደግ የጀመረውን የዘመናዊ ስቱዲዮ ግንባታ በአጋርነት ለመሥራት የሚያስችል ነው፡፡

05 Mar 2022

የ “ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል እንዳበረታታ ተገለፀ፡፡

ይህን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ10ኛ ዙር ያዘጋጀውን “የይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር ዕጣ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣበት ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ናቸው፡፡ የሽልማት መርሀ-ግብሩ በ2004 ዓ.ም መጀመሩን ያስታወሱት አቶ አቤ፣ ለ10 ዙር ሲካሄድ በርካቶችን ቁጠባን ባህላቸው ማድረግ ከማስቻሉም በላይ የትልልቅ ሽልማቶች እድለኛም እንዳደረገ ገልፀዋል፡፡ ባንኩ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር በህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ላይ ያመጣውን ተጽእኖ ለመፈተሸ ጥናት ማስጠናቱን አቶ አቤ የገለጹ ሲሆን፣ የጥናቱ ውጤትም በመርሀ-ግብሩ ሳቢያ ብዙ ደንበኞች በመደበኛነት እንዲቆጥቡና ቁጠባቸውንም ለረጅም ጊዜ ሳያወጡ እንዲቆዩ እንዳስቻላቸው ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

08 Feb 2022

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና የዋና መ/ቤት ሕንፃ ምርቃት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ተገለጸ፡፡ • ይህ የተገለፀው በአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 48ኛ ፎቅ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና የዋና መ/ቤት ሕንፃ ምርቃት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ተገለጸ፡፡ • ይህ የተገለፀው በአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 48ኛ ፎቅ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ ======== የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲሱን የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡ ሁነቱን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት ባንኩ ኢትዮጵያንም ሆነ ባንኩን በአፍሪካ በቀዳሚነት ከሚያስነሱ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን ሰማይ ጠቀስ ህንፃ በ80ኛ ዓመቱ ላይ እውን አድርጓል፡፡