05 Oct 2022
አፍሪካን ቢዝነስ ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2022 ባስመዘገበው አፈፃፀም በ929 ሚሊዮን ዶላር ካፒታል ከምስራቅ አፍሪካ ባንኮች መካከል በ3ኛ ደረጃ ተቀምጧል፡፡
05 Oct 2022
ይህ የተገለፀው ባንኩ በፕላቲኒየም ደረጃ ስፖንሰር ያደረገው የኢሬቻ ክብረ በዓል አካል በሆነውና በስካይላይት ሆቴል በተከናወነው 2ኛው የቱሪዝም ሽልማት እና የሚስ ቱሪዝም ኦሮሚያ የቁንጅና ውድድር ዝግጅት ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሱራ ሳቀታ በዝግጅቱ ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኦሮሞ ሕዝብ ታላቅ የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ የ2015 ዓ.ም ክብረ በዓል አካል በመሆኑ ታላቅ ክብር ተሰምቶታል፡፡
20 Aug 2022
ከነሀሴ 14 - ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል የሚካሄደው የአዲስ አመት ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተሳታፊዎች የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ‘Market Place’ አገልግሎትን በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው የመግቢያ ትኬት መቁረጥ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ተጀመረ።
15 Aug 2022
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2014 (2021/22) በጀት ዓመት 154.9 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ የተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘቡን 890.1 ቢሊዮን ብር ማድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስታውቀዋል፡፡ ባንኩ በበጀት ዓመቱ 27 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ከእቅዱ 16.3 በመቶ፣ ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ደግሞ የ43 ነጥብ 9 በመቶ ብልጫ እንደሚያሳይ አቶ አቤ ገልጸዋል።