19 Apr 2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ሀገራዊ እቅዱ እየተተገበረ ያለው በሪፎርም ማእቀፍ ውስጥ ከመሆኑ አንፃር እና ይህም ባንኩን በቀጥታ የሚመለከተው ከመሆኑ አንፃር በእቅድ አፈፃፀሙ ላይ ባንኩ ያለውን ድርሻ እና አበርክቶ እንዲሁም መልካም አጋጣሚ በሚገባ ተረድቶ ለቀጣይ ሥራ እንዲያግዝ ሪፖርቱ ላይ ውይይት ማድረግ ማስፈለጉን ገልፀዋል፡፡
05 Apr 2025
የደምበኞቻችንን የውጪ ምንዛሪ ጥያቄ ለመመለስ እ.ኤ.አ እስከ 31/03/2025 ድረስ ባጠቃላይ በቁጥር 711 ደንበኞቻችን ያቀረቡትን ጥያቄዎች በሙሉ በመገምገም ከቀረቡት ጥያቄዎች ውስጥ ብዛታቸው 698(98%) ለሆኑ ደንበኞች በድምሩ የ122.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድልድል የተደረገ መሆኑን እንገልጻለን።
04 Apr 2025
አቶ አቤ በዲጂታል አማራጭ ባለፉት ስምንት ወራት አጠቃላይ ብር 3.9 ቢሊዮን ብድር ማቅረብ የተቻለ መሆኑን ገልፀው፣ በዚህም እስከ ፌብርዋሪ 28 ቀን 2025 ድረስ 717 ሺህ ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
04 Apr 2025
በፌብሩዋሪ 2025 መጨረሻ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 1.541 ትሪሊዮን፣ ጠቅላላ የብድርና የቦንድ ክምችት መጠን ብር 1.393 ትሪሊዮን፣ እንዲሁም አጠቃላይ ሃብት ብር 2.073 ትሪሊየን መድረሱን አቶ አቤ በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡