መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ ቁጥር 1341/2016 መሰረት ባንኮች በሚሰጧቸው አገልግሎቶች ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲጣል ስለታወጀ ባንካችንም ይህንን የተጣለውን ግዴታ ለመወጣት ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ በባንካችን አገልግሎቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ቅድመ ማጣርያ የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ 1 ለ 0 በሆነ ጠባብ ውጤት ተሸንፏል፡፡ የመልስ ጨዋታው በቀጣዩ ቅዳሜ ዛንዚባር ላይ የሚደረግ ይሆናል።
በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን የወከለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ መስከረም 4 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በአበበ ቢቄላ ስታዲየም ከታንዛኒያው ያንግ አፍሪካንስ ጋር ይጫወታል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የዩጋንዳውን ኤስ ሲ ቪላ በድምር ውጤት 3 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉ ይታወቃል። መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን!
የሴካፋ ሀገራት ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን በባንካችን ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከሠራተኞች ጋር ደስታውን ተጋርቷል። **** ሻምፒዮኑ ቡድን በዋና ዋና የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በመዘዋወር ደስታውን ከህዝብ ጋር ተካፍሎ ዋናው መስሪያ ቤት ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። ቡድኑ ዋንጫውን ለባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስረክቧል። የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፉት አቶ አቤ፣ ለቡድኑ አባላት የአበባ ጉንጉን አበርክተዋል ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስን 1 ለ 0 በማሸነፍ የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ሻምፒዮን ሆኗል! በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከነሀሴ 11 ቀን 2016 ጀምሮ ሲካሄድ በቆየው በዚህ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ተወካዩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማሸነፉን ተከትሎ የሴካፋ ዞንን በመወከል በካፍ የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፍ ይሆናል፡፡
CBE Noor is one of the full-fledged interest free banking services. Designed to comply with the central tenets of Sharia (or Islamic law) of doing business.
The core processes of the bank entrusted with the task of international banking services. The services are now provided at all branches of the bank with a single contact point of customer service relationship officers assigned for this purpose only.
Delivering banking services through high level of process automated machines and web-based. It provides easy, convenient, flexible and secure banking services for CBE customers using their digital cards, mobile phone, or internet accesses.
ቪዛ ኢንተርናሽናል እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያደረጉት ስምምነት ለአምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን፤ ቪዛ ካርድን በብዛት ለ ኢ.ን.ባ ደንበኞች ለማቅረብ እና ለባንኩ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመስጠት እንደሚያስችል ለማወቅ ተችሏል
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳካው የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ፣ ለ7 ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮኑ የሴቶች ቡድን በሴካፋ ሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ መሆኑና ኢትዮጵያን በመወከል በፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 የተሳተፈችው የባንኩ አትሌት ፅጌ ዱጉማ የብር ሜዳሊያ ማምጣት መቻሏ ዓመቱን ልዩ እንደሚያደርገው አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል፡፡
አቶ አቤ ማእከሉ ከ7 ሺ 500 በላይ የሀገር ባለውለታ አረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማንን ከወደቁበት አንስቶ መጠለያ በመስጠት እና በመንከባከብ እየሠራ ያለው ሥራ ሊመሰገን እና ሊደገፍ የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮን ሆኗል! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስን 1 ለ 0 በማሸነፍ የካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ሻምፒዮን ሆኗል!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኬኒያው ኬኒያ ፖሊስ ቡሌትስ ሐሙስ ነሀሴ 23 ቀን 2016 ዓ/ም በአበበ በቂላ ስታዲየም በሚደረገው ፍፃሜ ጨዋታ ተፋላሚዎች ናቸው፡፡
ኤክስፖው ስያሜውን ያገኘበት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለአጠቃቅም ይበልጥ ምቹና የተለያዩ አማራጮችን የያዘ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ ሕብረተሰቡ ይህንኑ አገልግሎት እንዲጠቀም አበረታተዋል ።
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month