የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለ10 አመት የሚቆይ የ200 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረሙ፡፡ ========================= ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነቱን ለማሳደግ የጀመረውን የዘመናዊ ስቱዲዮ ግንባታ በአጋርነት ለመሥራት የሚያስችል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሰረት በርካታ የባንካችን ደንበኞች የግል መረጃቸውን ወቅታዊ በማድረግ ዕለታዊ የባንክ እንቅስቃሴአቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ። እርስዎም እስካሁን ባንክ የሚገኘውን የግል መረጃዎን ወቅታዊ ካላደረጉ፤ የታደሰ የነዋሪነት መታወቂያዎን በመያዝ አቅራቢያዎ በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመቅረብ መረጃዎን ወቅታዊ እንዲያደርጉ እናስታውስዎ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
ከታህሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 23 ቀን 2013 ዓ.ም ከ500 ብር ጀምሮ የቆጠቡና መስፈርቱን የሚያሟሉ ቆጣቢዎች በተሳተፉበት ዕጣ፣ 2 አፓርታማዎች፣ 10 አውቶሞቢሎች፣ 30 ባለ ሶሰት እግር ተሸከርካሪዎች እና 30 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ለእድለኞች ደርሰዋል፡፡ በዚህ መሠረት በ1ኛ ዕጣ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ሁለት ዘመናዊ አፓርታማ ቤቶች የሚያስገኙት የዕጣ ቁጥሮች 0275600863928 እና 1188200154301 በመሆን ወጥተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አዲሱ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መርቀዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲሱን የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡
CBE Noor is one of the full-fledged interest free banking services. Designed to comply with the central tenets of Sharia (or Islamic law) of doing business.
The core processes of the bank entrusted with the task of international banking services. The services are now provided at all branches of the bank with a single contact point of customer service relationship officers assigned for this purpose only.
Delivering banking services through high level of process automated machines and web-based. It provides easy, convenient, flexible and secure banking services for CBE customers using their digital cards, mobile phone, or internet accesses.
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና የዋና መ/ቤት ሕንፃ ምርቃት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚከናወን ተገለጸ፡፡ • ይህ የተገለፀው በአዲሱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ 48ኛ ፎቅ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡ ======== የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት የካቲት 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲሱን የዋና መ/ቤት ህንፃ ምርቃት በደማቅ ሥነ ሥርዓት እንደሚያከናውን አስታውቋል፡፡ ሁነቱን በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት ባንኩ ኢትዮጵያንም ሆነ ባንኩን በአፍሪካ በቀዳሚነት ከሚያስነሱ ፕሮጀክቶች አንዱ የሆነውን ሰማይ ጠቀስ ህንፃ በ80ኛ ዓመቱ ላይ እውን አድርጓል፡፡
ይህን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለ10ኛ ዙር ያዘጋጀውን “የይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር ዕጣ የካቲት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ባወጣበት ስነ-ስርአት ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ናቸው፡፡ የሽልማት መርሀ-ግብሩ በ2004 ዓ.ም መጀመሩን ያስታወሱት አቶ አቤ፣ ለ10 ዙር ሲካሄድ በርካቶችን ቁጠባን ባህላቸው ማድረግ ከማስቻሉም በላይ የትልልቅ ሽልማቶች እድለኛም እንዳደረገ ገልፀዋል፡፡ ባንኩ የ“ይቆጥቡ፤ ይሸለሙ!” መርሀ ግብር በህብረተሰቡ የቁጠባ ባህል ላይ ያመጣውን ተጽእኖ ለመፈተሸ ጥናት ማስጠናቱን አቶ አቤ የገለጹ ሲሆን፣ የጥናቱ ውጤትም በመርሀ-ግብሩ ሳቢያ ብዙ ደንበኞች በመደበኛነት እንዲቆጥቡና ቁጠባቸውንም ለረጅም ጊዜ ሳያወጡ እንዲቆዩ እንዳስቻላቸው ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለ10 አመት የሚቆይ የ200 ሚሊዮን ብር የስፖንሰርሺፕ ስምምነት በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራረሙ፡፡ ========================= ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል የተፈረመው ስምምነት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የአገልግሎት ጥራትና ተደራሽነቱን ለማሳደግ የጀመረውን የዘመናዊ ስቱዲዮ ግንባታ በአጋርነት ለመሥራት የሚያስችል ነው፡፡
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month