ትላንት ለገንዘብዎ ሁነኛ ባላደራ ሲፈልጉ በመላው ሀገራችን ቅርንጫፎቹን በመክፈት እርስዎ ወዳሉበት የደረሰው ባንካችን፣ ዛሬም በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ባለችው ዓለማችን፤ ከዘመኑ ጋር እየዘመነ አማራጮችዎን እያሰፋና ፍላጎትዎን እያሟላ በተለመደው ትጋቱ ቀጥሏል! ትጋት እና ጥረታችን ግብ መምታት ስኬቱ የሚለካው በርስዎ እርካታና ደስታ ነውና ለዚህ እውነት ቃላችንን ልናድስ "የላቀ አገልግሎት ደስተኛ ደንበኛ" በሚል መሪ ቃል የደንበኞች አገልግሎት ወርን እናከብራለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዘመናት በአብሮነት ለዘለቃችሁ ክቡራን ደንበኞቹ ምስጋናውን እያቀረበ ከታህሳስ 24 እስከ ጥር 25 የሚከበረው የደንበኞች አገልግሎት ወር የናንተ ነውና አብራችሁን እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። ከዚሁ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የጉዞ ሂደት የሚያሳይ አውደ-ርዕይ እና አዲሱን የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ከታህሳስ 24 እስከ ታህሳስ 30 በዋና መሥሪያ ቤታችን ተገኝተው እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
ምዝገባው ታህሳስ 15 /December 24, 2024/ ይጠናቀቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስያሜ ስፖንሰር የሆነበት ነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በየዙሩ 1.8 ሚልዮን ብር እንዲሁም ለአሸናፊዎች አሸናፊ 5 ሚሊዮን ብር ሽልማት፤ ምርጥ አምስት ዉስጥ ለሚገቡ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዣ የብድር እድል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያገኙበት የምእራፍ አራት ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት ብቻ ይቀራል፡፡ የሥራ ሀሳብዎን ወደ ነጋድራስ በማምጣትዎ ስራዎን ያስተዋዉቃሉ፤ ከአንጋፋ ዳኞች ጠቃሚ ምክር ያገኛሉ ፤ ያለማስያዣ የብድር ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡ ለመመዝገብ ሊንኩን (https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx) ይጠቀሙ፡፡ ይመዝገቡ ፤ ይወዳደሩ፤ ይሸለሙ!
ለክቡራን የባንካችን ደንበኞች ***** ባንካችን የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ በሚያደርግበት ወቅት ለክቡራን ደንበኞቹ ቀደም ብሎ እንደሚያሳውቅ ይታወቃል። በዚህ መሠረት ባንካችን በሚሰጣቸው የብድር፣ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል፣ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች ላይ በቅርቡ የብድር ወለድ እና የአገልግሎት ዋጋ ማሻሻያ የሚያደርግ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እናሳውቃለን። ******* የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር የቴሌቪዥን ፕሮግራም የስያሜ ስፖንሰር ነው። ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የምዕራፍ አራት ምዝገባ እየተካሄደ ነው። ነጋድራስ በየምዕራፉ 1.8 ሚሊየን ብር ይሸልማል። ለ አሸናፊዎች አሸናፊ ደግሞ 5 ሚሊዬን ብር ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምርጥ አምስት ውስጥ ለሚካተቱ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዥያ የብድር እንዲያገኙ አመቻችቶላቸዋል፡፡ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx ተመዝገቡ፣ ተወዳደሩ፣ አሸንፉ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸማ ተራ ቅርንጫፍ ተገልጋይ ደንበኞች በሙሉ ******************* ትናንት ምሽት (ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም) በተለምዶ ሸማ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በነባር የገበያ ማዕከል ሕንጻ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ጉዳት ምክንያት ሸማ ተራ ቅርንጫፋችን ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡ ከአደጋው ጋር በተያያዘም ወደ አዲስ ከተማ እና ሽንኩርት ተራ ቅርንጫፎቻችን የሚወስዱ መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተከትሎ ለዛሬ አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን ለውድ ደንበኞቻችን እንገልጻለን፡፡ በመሆኑም ደንበኞቻችን፡- 1. ሳህን ተራ 2. መሀል ገበያ 3. ጎማ ተራ 4. ቦምብ ተራ 5. መርካቶ 6. ሁነኛው መራ 7. ሸራ ተራ 8. ሳጥን ተራ 9. ሲዳሞ ተራ እና ሌሎች በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ እናስታውቃለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
CBE Noor is one of the full-fledged interest free banking services. Designed to comply with the central tenets of Sharia (or Islamic law) of doing business.
The core processes of the bank entrusted with the task of international banking services. The services are now provided at all branches of the bank with a single contact point of customer service relationship officers assigned for this purpose only.
Delivering banking services through high level of process automated machines and web-based. It provides easy, convenient, flexible and secure banking services for CBE customers using their digital cards, mobile phone, or internet accesses.
በውይይቱ የተሳተፉ ደንበኞች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጊዜ ወደ ጊዜ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ዲኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ትልቅ እና የሀገር ባለውለታ አንጋፋ ባንክ መሆኑን ገልፀው የደንበኞች የውይይት መድረኩን ማዘጋጀቱም የሚያስመሰግነው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዲላ ከተማ የደንበኞች የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
አቶ ኤፍሬም የባንኩ የትኩረት አቅጣጫ የደንበኞችን አገልግሎት ማሻሻል መሆኑን ገልፀው፣ ባንኩ ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ከባንኩ ጋር በታማኝነት እየሠሩ ላሉት ደንበኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት "የላቀ አገልግሎት ፣ ደስተኛ ደንበኛ" በሚል መሪ ቃል የደንበኞች አገልግሎት ወር እያከበረ ይገኛል።
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month