04 Jan 2025
የብድር ማስያዣ ንብረት ግምት፣ የብድር አሰጣጥ ሂደት፣ ለወጭ ንግድ የሚሰጡ አገልግሎቶች፣ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት፣ የአገልግሎት ክፍያ እና ሌሎችም በውይይቱ ትልቅ ትኩረት ያገኙ ጉዳዮች ነበሩ፡፡
04 Jan 2025
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካስተመር ኤክስፔሪያንስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ በቀጣይ የደንበኞች አገልግሎት ወር ከአለም አቀፍ የደንበኞች አገልግሎት ሳምንት ጋር በማስተሳሰር በየዓመቱ በጥቅምት ወር በተጠናከረ ሁኔታ በባንኩ እንደሚከበር ገልፀዋል፡፡
04 Jan 2025
የባንካችን ደንበኞች ብቻ ሳትሆኑ ቤተሰብም በመሆናችሁ ስለአገልግሎት አሰጣጣችን የምትሰጡንን ሀሳብ እና አስተያየት አክብረን እንቀበላልን፡፡ ለተግባራዊነቱም አበክረን እንሠራለን፡፡ የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች ከናንተ ከደንበኞቻችን ጋር በመሆን ወደምቹ አጋጣሚ እየቀየርን እድገታችንን እናስቀጥላለን፡፡
04 Jan 2025
የኢፌዲሪ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ባንኩ ፈተናዎችን አልፎ ዛሬ ለደረሰበት ስኬት የደንበኞች አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፣ “እምነታችሁን ስለሰጣችሁን እና ከባንካችን ጋር ስለምትሠሩ እናመሰግናለን’’ በማለት ለባንኩ ደንበኞች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡