News Archive

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተፈረመው ይህ ስምምነት 26 የሚሆኑ የፌዴራል የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እና በስራቸው የሚገኙ 360 ተቋማት ለተገልገዮች የሚሰጧቸው አገለግሎቶችን ክፍያ በዲጂታል አማራጭ የሚቀበሉበትን መንገድ ያመቻቸ መሆኑ ተገልጿል፡፡

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን አስመልክቶ በሠመራ ከተማ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ-ግብር አከናወነ።

የአል ሃምዱ የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቅርንጫፍም ተመርቆ ሥራ ጀምሯል፡፡

13 Dec 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀናጀ የሥራ ላይ ሥልጠና ለተሳተፉ የቦሌና ቂርቆስ ዲስትሪክት ሠራተኞች ዕውቅና ሰጠ፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰው ኃይል ልማት ዳይሬክተር ወ/ሮ እየሩሳሌም አመሃ በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት የተካሄደውን የዕውቅና አሰጣጥ መርሃ ግብር በንግግር በከፈቱበት ወቅት እደተናገሩት፣ የተቀናጀ የሥራ ላይ ስልጠና ፕሮግራም የባንኩን የስልጠና አካሄድ በመለወጥ አይነተኛ ሚና አለው፡፡

29 Nov 2024

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ ግሬት ራን ጋር በመተባበር በእንጦጦ ፓርክ የሚደረገውን ወርሃዊ የሩጫ ውድድርን (ENTOTO PARK CBE RUN) ስፖንሰር አደረገ፡፡ • የመሮጫ ትኬቱ በሲቢኢ ብር ይቆረጣል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አቶ ደረጄ ፉፋ እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች አንዱ የስፖርቱን ዘርፍ መደገፍ ነው፡፡