aboutሲቢኑርሲቢኑር
ሲቢ ኑር ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ሲሆን በመደበኛው የባንክ አገልግሎቶች ላይ በፍላጎትም ዪሁን በሀይማኖት ምክንያት አገልግሎቱን ማግኝት ላልቻሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የቀረበ ሁሉን አቀፍ የባን አገልግሎት ነው፡፡ ይህም አገልግሎት የተመሰረተው በሸሪያ የንግድ እንቅስቃሴ ሕግ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/72/2019 መሰረት ነው፡፡
- ትርፍ መጋራት (የትርፍ ክፍያን ተመጣጣኝ ለማድረግ የሚያዝ መጠባበቂያ ካፒታል)፡- ይህ መጠባበቂያ ካፒታል ለደንበኞች የሚከፈለው የትርፍ ክፍያ ከኢንዱስትሪው የገበያ ዋጋ በላይ ሲሆን ለሌላ ጊዜ ለሚደረጉ የትርፍ ክፍያዎች ዘላቂነት በየጊዜው ከሚገኘው የተጣራ ገቢ ተቀናሽ ተደርጎ የሚያዝ ነው፡፡ ስለሆነም ትርፉ አመርቂ በሆነ ጊዜ በባንኩ በተወሰነው መሠረት መጠባበቂያ ገንዘብ የሚያዝ ሲሆን፣ ትርፉ በቀነሰ ጊዜ ከመጠባበቂያ ገንዘብ ላይ በመቀነስ ለደንበኞች የሚከፈል ይሆናል፡፡
- የትርፍ ክፍፍል፡-በሙዳረባህ የቁጠባ ሂሳብ እና በሙዳረባህ የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞቻችን ከባንኩ ጋር ትርፍ ወይም ኪሣራ የሚጋሩ ሲሆን፣ የትርፍ ክፍፍሉም የሚከናወነው ባንኩ በሠጠው ፋይናንስ ላይ ከሚገኘው ትርፍ ታሳቢ ይሆናል። ነገር ግን ባንኩ ለሚሠጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ከደንበኞች የሚያገኛቸው ገቢዎች ለምሳሌ ከኮሚሽንና ከአገልግሎት የሚገኘው ትርፍ የባንኩ ትርፍ ሲሆን ይህንን ባንኩ ለደንበኞች አያካፍልም፡፡