የጀመርነውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመጨረስ ስጦታዎን በሞባይል መተግበሪያ ItsMyDam ያበርክቱ፡፡ መተግበሪያውን ለማውረድ https://play.google.com/store/apps/details... https://apps.apple.com/us/app/itismydam/id1576556192 ድረ-ገጽ https://itismydam.et/ #GERD #CBE
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አመራርና ሠራተኞች በተከበሩ ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻሉ፡፡ አፍሪካዊቷ ማዘር ቴሬዛ በመባል የሚታወቁት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በ1928 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ በግራር ጃርሶ ወረዳ በቶርበን አሼ ቀበሌ ገበሬ ማሕበር ተወለዱ ፡፡ ዶ/ር አበበች ጎበና የአገር ባለውለታነት አልፈው ለሰው ልጆች ትልቅ ክብርን በመስጠት ወላጅ ለሌላቸው እናትም፣ አባትም ሆነው ሰው ከወደቀበት ቀና እንዲል በማድረግ ብዙ መቶ ሺህ ህፃናትን ተንከባክበው ለቁም ነገር ያበቁ የሀገር ባለውለታ ነበሩ፡፡ ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ85 አመታቸው ሰኔ 27 ቀን 2013 ዓ.ም ህይወታቸው አልፏል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አመራርና ሠራተኞች በተከበሩ ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፁ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው ኢትዮጵያውያን መፅናናትን ይመኛሉ፡፡
በቅርቡም በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ማስታወቂያ በማውጣት አመልካቾችን ለመቀበል ጥረት እያደረገ ሲሆን፣ ከሌላው ጊዜ በተለየ እጅግ በርካታና በብዙ ሺ የሚቆጠሩ አመልካቾች በአንድ ጊዜ ወደ ሲስተም የሚገቡ በመሆኑ አሁን ላይ በሲስተም ላይ መጨናነቅና ጫና እያጋጠመ በመሆኑ ማመልከቻዎቻችሁን መቀበል የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግ እና በተለያዩ ቀናት ከእናንተ ከአመልካቾቻችን የደረሱንን ጥቆማዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ጫና ላይ የወደቀውን ሲስተም አስተካክልን ሳትጉላሉ ማመልከቻዎቻችሁን በቀላሉ ማስገባት የሚያስችል ጥረት እያደረግን በመሆኑ በቅርቡ ማስተካከያዎችን አድርገን የማመልከቻ ቀን የምናራዝም መሆናችንን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ የሥራ ማመልከቻ ያልተሳካላችሁ በቀጣይ ማመልከት እንድትችሉ የባንኩ የማህበራዊ የትስስር ገፆችን ጨምሮ በሌሎች ሚዲያዎች ወደፊት የምናሳውቅ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን፡፡
ለውድ የባንካችን ዌብሳይት ተጠቃሚዎች፡- የባንካችንን ዌብሳይት የማዘመንና ለተጠቃሚዎች ይበልጥ አመቺ የማድረግ ሥራ በመስራት ላይ ስለሆን፣ ዌብሳይቱ ላይ ላልተወሰኑ ጥቂት ቀናት ለተጠቃሚዎች አመቺ የማይሆንበት አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በመሆኑም ዌብሳይቱን የማዘመን ስራ በፍጥነት እንደሚጠናቀቅ እየገለፅን፣ በዚሁ ምክንያት ለሚፈጠረው መስተጓጎል ከወዲሁ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚከተሉትን እቃዎች ከሀገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ለበለጠ መረጃ ይህን የጫኑ https://combanketh.et/commercial-bank-of-ethiopia/tenders/
ሲቢ ኑር ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ሲሆን በመደበኛው የባንክ አገልግሎቶች ላይ በፍላጎትም ዪሁን በሀይማኖት ምክንያት አገልግሎቱን ማግኝት ላልቻሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የቀረበ ሁሉን አቀፍ የባን አገልግሎት ነው፡፡ ይህም አገልግሎት የተመሰረተው በሸሪያ የንግድ እንቅስቃሴ ሕግ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/72/2019 መሰረት ነው፡፡
የንግድ አገልግሎቶች
ዲጂታል የባንክ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይህን ያስታወቀው የሀገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ለተሰማራው መከላከያ ሰራዊትና ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ላሉ የክልል ልዩ ኃይሎችና የአካባቢ ሚሊሺያዎች የሚያደርጉትን ተጋድሎ መደገፉን አስመልክቶ ነሀሴ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው። በተገባደደው 2013 ዓ.ም በተለያዩ የባንክ አገልግሎት ዘርፎች የተሻለ አፈፃፀም የተመዘገበበት እንደነበር ያስታወቁት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ከ140 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በማሰባሰብ በታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ማሳካት የቻለበት ዓመት ነበረም ነው ያሉት።
“ኢትዮጵያን እናልብስ” በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ በሚካሄደውና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ማኔጅመንትና ሠራተኞች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ620 ሺህ በላይ ችግኞችን ተክለዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በአይ.ሲ.ቲ ፓርክ ጊቢ ውስጥ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባደረጉት ንግግር ባንኩ በደን ልማትና በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ ላለፉት አመታት በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን ገልጸው፣ ዘንድሮም ለሶስተኛ ጊዜ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ላይ መሳተፉን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2020/21 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀሙን እና የ2021/22 በጀት ዓመት ዕቅዱን ላለፉት ጥቂት ቀናት ሲገመግም የቆየ ሲሆን ሀምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የማጠቃለያ መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡ በማጠቃለያ መርሀ-ግብሩ የላቀ አፈፃጸም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶችና የሪጅን ጽ/ቤት የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዳለፉት በርካታ ዓመታት ሁሉ የባንክ አገልግሎትን በመላ ሀገሪቱ በማስፋፋት ፣ የክፍያ ስርዓቱን በማዘመን፣ደንበኞችን መሠረት ያደረጉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን በማቅረብ እና የሀገሪቱን ልማት በመደገፍ ውጤታማ አመት ማሳለፉ በማጠቃለያ መርሀ-ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳስታወቁት በአንድ አመት ብቻ 140 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ ሲሰበሰብ በባንኩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡ በተመሳሳይም በአመቱ ባንኩ ካደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ በማሰመዝገብ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል፡፡ የሀገሪቱን የልማት እንቅስቃሴ በአግባቡ ለመደገፍ ወሳኝ የሆነውን የውጪ ምንዛሬ ግኝት ለማሳደግ በተደረገው ጥረትም በበጀት አመቱ ከ2.86 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ከተለያዩ ምንጮች መሰብሰብ ተችሏል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኘሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ሙፍቲ ሃጅ ዑመር እድሪስ ለአንድ ወር በሚቆየው የለበይክ የቁጠባ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ወቅት እንዳሉት ማንኛውም ሙስሊም ሐጅ ለማድረግ መቆጠብ አለበት ብለዋል፡፡ ቁጠባ የግል ህይወትን ለመቀየርም፣የተሳካለት የቢዝነስ ሰው ለመሆንም ወሳኝ ነው ያሉት ሙፍቲ ሃጂ እድሪስ ከምንም በላይ እያንዳንዱ ሙስሊም በህይወት ዘመኑ ሐጅ የማድረግ ግዴታን ለመወጣት ባንኩ በአማራጭነት ያቀረበውን የለበይክ ቁጠባ ሒሳብ በመክፈት ሳይቸገሩ ሐጅ ማድረግ ጥሩ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ጎልፍ ማህበር ጋር በመተባባር የተዘጋጀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2013 ዓ.ም የጎልፍ ጨዋታ ውድድር በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ውድድሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ አስጀምረዋል፡፡ ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከሚያደርጋቸው ተግባራት መካከል የህብረተሰቡን ጤና ከማስጠበቅ አንፃር ከፍተኛ ጠቀሜ ያላቸውን ስፖርታዊ ውድድሮች መደገፍ መሆኑን አቶ አቤ የጎልፍ ጨዋታ ውድድሩን ባስጀመሩበት ወቅት ተናግረዋል፡፡ የጎልፍ ጨዋታ በሀገራችን ከተጀመረ ረዘም ያለ ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም በብዛት ሲዘወተር እንደማይታይ የገለጹት አቶ አቤ ስፖርቱን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል፡፡
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month