ትላንት ለገንዘብዎ ሁነኛ ባላደራ ሲፈልጉ በመላው ሀገራችን ቅርንጫፎቹን በመክፈት እርስዎ ወዳሉበት የደረሰው ባንካችን፣ ዛሬም በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ባለችው ዓለማችን፤ ከዘመኑ ጋር እየዘመነ አማራጮችዎን እያሰፋና ፍላጎትዎን እያሟላ በተለመደው ትጋቱ ቀጥሏል! ትጋት እና ጥረታችን ግብ መምታት ስኬቱ የሚለካው በርስዎ እርካታና ደስታ ነውና ለዚህ እውነት ቃላችንን ልናድስ "የላቀ አገልግሎት ደስተኛ ደንበኛ" በሚል መሪ ቃል የደንበኞች አገልግሎት ወርን እናከብራለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዘመናት በአብሮነት ለዘለቃችሁ ክቡራን ደንበኞቹ ምስጋናውን እያቀረበ ከታህሳስ 24 እስከ ጥር 25 የሚከበረው የደንበኞች አገልግሎት ወር የናንተ ነውና አብራችሁን እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። ከዚሁ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የጉዞ ሂደት የሚያሳይ አውደ-ርዕይ እና አዲሱን የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ከታህሳስ 24 እስከ ታህሳስ 30 በዋና መሥሪያ ቤታችን ተገኝተው እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
ምዝገባው ታህሳስ 15 / December 24, 2024/ ይጠናቀቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስያሜ ስፖንሰር የሆነበት ነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በየዙሩ 1.8 ሚልዮን ብር እንዲሁም ለአሸናፊዎች አሸናፊ 5 ሚሊዮን ብር ሽልማት፤ ምርጥ አምስት ዉስጥ ለሚገቡ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዣ የብድር እድል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያገኙበት የምእራፍ አራት ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት ብቻ ይቀራል፡፡ የሥራ ሀሳብዎን ወደ ነጋድራስ በማምጣትዎ ስራዎን ያስተዋዉቃሉ፤ ከአንጋፋ ዳኞች ጠቃሚ ምክር ያገኛሉ ፤ ያለማስያዣ የብድር ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡ ለመመዝገብ ሊንኩን (https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx) ይጠቀሙ፡፡ ይመዝገቡ ፤ ይወዳደሩ፤ ይሸለሙ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር የቴሌቪዥን ፕሮግራም የስያሜ ስፖንሰር ነው። ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የምዕራፍ አራት ምዝገባ እየተካሄደ ነው። ነጋድራስ በየምዕራፉ 1.8 ሚሊየን ብር ይሸልማል። ለ አሸናፊዎች አሸናፊ ደግሞ 5 ሚሊዬን ብር ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምርጥ አምስት ውስጥ ለሚካተቱ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዥያ የብድር እንዲያገኙ አመቻችቶላቸዋል፡፡ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx ተመዝገቡ፣ ተወዳደሩ፣ አሸንፉ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከተሉትን የግል መረጃ ደኅንነት ምክሮች እንድትተገብሩ በጥብቅ እናሳስባለን! • የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ በሚያደርጉት ነገር ላይ ብቻ ያተኩሩ፤ ትኩረትዎን የሚያስተጓጉሉ እንደ ሞባይል ስልክ እና መሰል ነገሮቸን አይጠቀሙ፡፡ • የሚስጢር ቁጥርዎን እየቀየሩ ይያዙ ፤ በሚቀይሩበትም ጊዜ ከማንኛውም የግል መረጃ ለምሳሌ የልደት ቀኖች፣ የስልክ ቁጥሮች ጋር አያገናኙ፡፡ • የተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የሚጭኗቸውን መተግበሪያዎች ሲያወርዱ አፕስቶር ፣ ፕሌይስቶርን ብቻ ይጠቀሙ፡፡ • ደኅንነቱ ያልተረጋገጠ ድረ-ገጽ እና የማኅበራ ሚዲያ ገጿችን አይጠቀሙ፡፡ • ግብይትዎን በሚያካሂዱበት ጊዜ ችግር ቢያጋጥሞ ከሚመለከታችው የባንኩ ሠራተኞች ውጪ የማንንም እገዛ አይጠይቁ፡፡ • የኤ.ት.ኤም ማሽን ላይ ሲጠቀሙ የሚስጢር ቁጥሮ እንዳይታይ፤ የኤቲኤም ቁልፍ ሰሌዳውን ሰውነትዎን ተጠቅመው በመሸፈን፤ በቅርብ የቆሙ ሰዎች እንይመለከቱ ይከላከሉ፡፡ • ከግብይት በኋላ ካርዱን መቀበሎን ያረጋግጡ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስልክ በመደወልም ሆነ በጽሁፍ መልዕክት በመላክ የባንክ አገልግሎት ስለማይሰጥ፤ ከዚህ መሰል መጭበርበሮች እንድትጠነቀቁ ያሳስባል! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የጀመርነውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለመጨረስ ስጦታዎን በሞባይል መተግበሪያ ItsMyDam ያበርክቱ፡፡ መተግበሪያውን ለማውረድ https://play.google.com/store/apps/details... https://apps.apple.com/us/app/itismydam/id1576556192 ድረ-ገጽ https://itismydam.et/ #GERD #CBE
ሲቢ ኑር ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ሲሆን በመደበኛው የባንክ አገልግሎቶች ላይ በፍላጎትም ዪሁን በሀይማኖት ምክንያት አገልግሎቱን ማግኝት ላልቻሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የቀረበ ሁሉን አቀፍ የባን አገልግሎት ነው፡፡ ይህም አገልግሎት የተመሰረተው በሸሪያ የንግድ እንቅስቃሴ ሕግ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/72/2019 መሰረት ነው፡፡
የንግድ አገልግሎቶች
ዲጂታል የባንክ አገልግሎት
የሲቢኢ ብር ደንበኞች በ847 አጭር የጥሪ መስመር ላይ በመደወል ለብቻ እንዲስተናገዱ በአዲስ መልክ መዘጋጀቱንና ፖስ ማሽን የሚያስጠቅሙ ኮርፖሬት ደንበኞች ደግሞ በ915 አጭር የጥሪ መስመር ላይ በመደወል እንዲስተናገዱ መዘጋጀቱንም አቶ አብይ ገልፀዋል።
የባንኩ ከስተመር ኤክስፔሪየንስ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሃይለእየሱስ በቀለ ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር በሚያደርገው ውይይት ከደንበኞቹ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችለውን ግብአት እያገኝ ነው ብለዋል።
አቶ ኤፍሬም የባንኩ የትኩረት አቅጣጫ የደንበኞችን አገልግሎት ማሻሻል መሆኑን ገልፀው፣ ባንኩ ደንበኛን ያማከለ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ከባንኩ ጋር በታማኝነት እየሠሩ ላሉት ደንበኞች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት "የላቀ አገልግሎት ፣ ደስተኛ ደንበኛ" በሚል መሪ ቃል የደንበኞች አገልግሎት ወር እያከበረ ይገኛል።
አቶ አቤ ሳኖ የ15 ዓመት አገልግሎት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month