ሞባይል ባንኪንግ *889#

1. በተንቀሳቃሽ ስልክ አማካይነት የሚሰጥ የባንክ አገልግሎት ነው፤ 2. አገልግሎቱም በዩ ኤስ ኤስ ዲ፣ በኢንተርኔት ወይም ለባንክ አገልግሎት በተዘጋጀ መተግበሪያ በሚደረግ ተግባቦት ሊከናወን ይችላል፤ 3. ደንበኞች የሚከተሉትን ተግባራት እንዲያከናውኑ ያስችላል፡- • የቁጠባ ወይም ተንቀሳቃሽ ሒሳቦቻቸውን እንዲያስተዳድሩ፤ • ከራሳቸው ሒሳብ ወደ ተጠቃሚያቸው ወይም ወደ ሌላ የባንኩ ሒሳብ ያለው ደንበኛ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ።

Download our app:

የሞባይል ባንኪንግ ቻናሎች

picture

ለገንዘብ ዝውውር

  • ደንበኞች ከሒሳባቸው ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ አሊያም ወደ ሌሎች የግል ባንኮች ሒሳብ በቀላሉ ማስተላለፍ ያስችላል።

የቴሌኮም አየር ሰዓት ለመሙላት

  • ደንበኞች ከሞባይል ባንክ አገልግሎታቸው በቀጥታ የኢትዮ ቴሌኮምን አሊያም የሳፋሪ ኮምን የስልክ የአየር ሰዓት በቀላሉ መሙላት ይችላሉ።

የአገልግሎት ክፍያዎችን ለመክፈል

  • ደንበኞች የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን ማለትም የመብራት፥ የስልክ፥ የውሃ እና የመሳሰሉትን በቀላሉ በእጃቸው ባለው ስልክ መክፈል ይችላሉ።

የመንግስት አገልግሎቶችን

  • በሞባይል ባንኪንግ በመጠቀም ደንበኖች የመንግስትን አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት እና ክፍያዎችን ለመፈጸም ያስችላቸዋል። ለምሳሌ ግብርን ለመክፈል፤ ለፓስፖርት ክፍያ፤ እና ለመሳሰሉት

ቀጥታ ክፍያዎችን ለመፈጸም

  • ደንበኞች በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በመጠቀም ለትምህርት ቤት ክፍያዎችን፥ለጤና ተቋማት ክፍያ፥ ገንዘብ ለመለገስ፥ ዲጂታል እቁብ ለመጣል እና ለመሳሰሉት

ለጉዞ ክፍያ

  • ደንበኞች ለጉዞ የሚሆን ክፍያን ለመፈጸም የአየር ትኬቶችን ለመቁረጥ፥ ለራይድ ለመክፈል እና ለመሳሰሉት ያስችላል።

የሞባይልባንኪንግ ዋናዋና አገልግሎቶች

  • የሞባይል ባንክ አገልግሎት ማለት ደንበኞች በተንቀሳቃሽ ስልካቸው/Mobile phone/በመታገዝ የባንክ ሂሳባቸውን የሚያንቀሳቅሱበት አገልግሎት ነው። አገልግሎቱንም ሳምንቱን ሙሉ የ24 ሰዓት የባንክ አገልግሎት ያገኛሉ። የሞባይልባንኪንግ ዋናዋና አገልግሎቶችም 1. ገንዘብ ማስተላለፍ:-ይህ አገልግሎት ደንበኞች ከሒሳባቸው ወደ ሌላ ሒሳብ ወደማንኛውም ንግድ ባንክ ሒሳብ፣ ወደ ግል ሒሳብ፣ ወደ ሲቢኢብርና ቴሌብር ዋሌት፣ ወደ ሲቢኢብርና ቴሌብር ኤጀንት፣ ወደ ሌሎች ባንኮች እንዲሁም ወደ ተመረጡ ማይክሮፋንናንስ ተቋማት ገንዘባቸውን የሚያንቀሳቅሱበት ነው። 2. የቴሌኮም አገልግሎት:-ይህ አገልግሎት ደንበኞች የኢትዮቴሌኮምና ሳፋሪ ኮም ቅድመ ክፍያና ድህረክፍያዎችን የሚፈፅሙበት ነው። 3. ፍጆታ:- ይህ አገልግሎት ደንበኞች ለተጠቀሙት የውሀ የመብራትና ሌሎች ክፍያዎችን ካሉበት ሆነው የሚከፍሉበት ነው። 4. የመንግስት ተቋማት ክፍያ:-ይህ አገልግሎት ደንበኞች ለተለያዩ የመንግስት ተቋማት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ለመክፈል ያስችላቸዋል፡ ከነዚህም ውስጥ አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች፣ ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ሶማሊያ ገቢዎች ቢሮ ግብር ክፍያ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ የፓስፖርትና የመኖሪያ ፈቃድ ክፍያን ካሉበት ሆነው በእጅ ስልካቸው የሚከፍሉበት ነው። 5. ክፍያዎች:-ይህ አገልግሎት ደንበኞች ያሉባቸውን እዳዎች (የነጋዴ ክፍያ፣ የትምህርት ቤትክፍያ፣ የጤና ክፍያ፣የእርዳታ ድርጅቶች ልገሳ፣ ድጅታል እቁብ) በቀላሉ ለመክፈል ያስችላቸዋል። 6. ጉዞ:-ይህ አገልግሎት ደንበኞች ለተለያዩጉዳዮች ለሚኖራቸው ጉዞ የምድርና የአየርትራን ስፖርትትኬትን ካሉበት ሆነው በቀላሉ ለመቁረጥ ያስችላቸዋል። 7. መዝናኛ:-ይህ አገልግሎት ደንበኞች ለCanal+ እንዲሁም የዲኤስቲቪ አገልግሎት ክፍያዎችን ለመክፈል የሚያስችል አገልግሎት ነው። 8. ባንኪንግ:-ይህ አገልግሎት ደግሞ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች (ቋሚ ትዕዛዝ መስጠትና መሰረዝ፣ አዲስ ካርድና ቅያሪ ማዘዝ፣ የእለቱን የምንዛሬ ተመንማየት፣ ATM ፡ የባንኩን ቅርንጫፍ ፡ ሲቢኢብር ወኪሎች፡ ነጋዴ ፖስ መገኛን ማወቅ እንዲሁም ጥያቄ መጠየቅ) የሚያገኙበት ነው።

ከሞባይል ባንኪንግ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ደንበኞች የሚከተሉትን አገልግሎቶች በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፎችና የደንበኞች ግንኙነት ማዕከል 951 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

  • • ቻናል ማስጨመር: አንድ ብቻ ቻናል ያላቸው ደንበኞች ተጨማሪ ቻናል ሲፈልጉ እንዲጨመርላቸዉ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ • የአገልግሎት ማብቂያ ቀንን ማስተካከል፡ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ቀኑ ያለፈባቸው ደንበኞች የአገልግሎት ቀኑ እንዲራዘምላቸዉ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ ማመልከት ይችላሉ፡፡ • ቻናል ዳግም ለማስጀመር፡ የሚስጢር ቁጥራቸውን የረሱ ደንበኞች በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በመገኘት የፒን ቁጥር ዳግም ለማስጀመር መጠየቅ ይችላሉ፡፡ • ስልክቁጥርለመቀየር፡ ስልክ ቁጥራቸውን መቀየር የፈለጉ ደንበኞች እንዲቀየርላቸዉ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ ማመልከት ይችላሉ፡፡ • ስልክ ቀፎ ለመቀየር፡ ሞባይል ቀፎመቀየር የፈለጉ ደንበኞች እንዲቀየርላቸዉ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ ማመልከት ይችላሉ፡፡ • የሞባይል ባንኪንግን አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ ለማገድ፡ ደንበኞች ሞባይል ስልካቸውን ከተሰረቁ ወይንም ከጠፋባቸው ወዲያውኑ በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት ወይም 951 በመደወል በጊዚያዊነት አገልግሎቱን ለማሳገድ ማመልከት ይችላሉ፡፡ • የተቋረጠውን የሞባይልባንኪንግን አገልግሎት ለማስጀመር፡ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎታቸውን በጊዚያዊነት ያሳገዱ ደንበኞች አገልግሎቱን ዳግም ለማስጀመር በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ ማመልከት ይችላሉ፡፡ • ተጨማሪ አካውንት ለማጣመር፡ ደንበኞች በአንድ መለያ ቁጥር ያሉ ተጨማሪ አካውንቶችን በአንድ ሞባይል ባንኪንግ ለማጣመር ማመልከት ይችላሉ፡፡

ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ያለዎትን ማንኛውንም ቅሬታ ወይም አስተያት በሚከተሉት አማራጮች ማሳወቅ ይጭችላሉ፦

  • 1. ቅሬታውን ለፈጠረው ቅርናጫፍ ሥራ-አስኪያጅ በቀጥታ፣ 2. የደንበኞች አገልግሎት ማዕከል ነፃ የስልክ ጥሪ 951 በመደወል፣ 3. የባንኩን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ/Application/ በመጠቀም “አስተያየትመስጫ” የሚለውን አማራጭ በመጠቀም ቅሬታዎን ወይም ሃሳብ አስተያየትዎን በመፃፍ መላክ ይችላሉ። በተጨማሪም፦ ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘት እንዲችሉ የባንካችንን ትክክለኛ የቴልግራም ገፅ https://t.me/combankethofficialይቀላቀሉ።