የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ
• ባንኩ ለሻጭ በጽሑፍ የሚገባው ውል ነው፤ • ውሉ የሚገባው በገዥ ጥያቄ ወይም ትእዛዝ መሠረት ባንኩ ለሻጭ ክፍያ ይፈጽም ዘንድ ወይም ሻጩ የሽያጭ ሰነዱን (ድራፍት) ሲያቀርብ ነው፤ • ውሉ የሚከፈለውን የገንዘብ መጠን እና የተቀመጠለትን የጊዜ ገደብ ከተጨማሪ ሰነዶች ጋር በማመሳከር ይገልጻል።
• ባንኮች የሻጮችን የንግድ ሰነዶች (ከገንዘብ ነክ ሰነዶች ጋር ወይም ያለ ገንዘብ ሰነዶች) ከእነሱ በሚሰጣቸው ትእዛዝ መሠረት የሚያንቀሳቅሱበት አሠራር ነው፤ • ባንኮች ሰነዶችን ለገዢዎች (አስመጪዎች) እንዲያቀርቡ የሚያደርግ አሠራር ሲሆን ይህም ገዢዎች ክፍያ ሲፈጽሙ (ወይም ሳይፈጽሙ) ወይም በሌሎች ዉሎች እና መስፈርቶች መሠረት ይከናወናል።
የቅድመ ክፍያ አገልግሎት (ሻጩ እንዲላኩ የተወሰኑትን እቃዎች ወይም አገልግሎቶች ለገዢው ከማድረሱ በፊት ክፍያ የሚያገኝበት መንገድ)
• እቃዎች በውጭ አገር በሚገኝ ወኪል (አከፋፋይ) አማካይነት እስከሚሸጡ ድረስ የእቃዎቹ ባለቤትነት ከሻጩ ጋር የሚቆይበት የክፍያ መንገድ ነው፤ • ወኪሉ (አከፋፋዩ) ሸቀጦቹን የሸጠ እንደሆነ ብቻ ሻጩ ክፍያውን ሊቀበልበት ይችላል።
• አንድ ባንክ/ዋስትና ሰጪ ለተጠቃሚው (በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ አገር ላለ) የዋስትና ደብዳቤ የሚሰጥበት አገልግሎት ነው፤ • ግዴታዉን መፈጸም ያለበት አካል ግዴታውን በተቀመጠው ዉል መሠረት ሳይፈጽም በሚቀርበት ጊዜ ተጠቃሚው በተስማማበት ውል/ሰነድ መሠረት እንዲካስ (የተጠቀሰው ገንዘብ መጠን እንዲከፈለው) ለማድረግ የታቀደ ነው፤
የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ (አስመጪዎች የውጭ ምንዛሬ መክፈል ሳያስፈልጋቸው ሸቀጦችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እንዲችሉ የሚሰጥ ፈቃድ)
አነስተኛ የወጪ ንግድ እቃዎች የማስወጣት ፈቃድ (የውጭ አገር ጎብኝዎች ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የስጦታ እቃዎችን፤ ሳምፕሎችን፤ ስጦታዎችን፤የሚጠገኑ እቃዎችን፤ የኢግዚቢሽን እቃዎችን እና የግለሰቦች መገልገያ እቃዎችን የመሳሰሉ አነስተኛ እቃዎችን ያለ ቀረጥ ከአገር ማስወጣት እንዲችሉ የሚሰጥ ፈቃድ)።