የብድር አገልግሎት

የብድር አገልግሎት ከቀዳሚ የባንክ አገልግሎቶች ማካከል አንዱ ሲሆን ለባንኩም ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሚያስገኝ የአገልግሎት ዓይነት ነው፡፡ ብድር የስራ ዕድል በመፍጠር ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገቶችን በማምጣት ለሀገር እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወት የአገልግሎት ዓይነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ለኢንቨስትመንት የሚሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ብድር በማመቻቸት ለሀገር እድገት አስተዋጽዎ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

General Eligibility Criteria for Loan Application

የብድር ዓይነቶች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ

የመዋዕለ ንዋይ ፍሰት/ለኢንቨስትመንት

'

  • የጊዜ ገደብ ብድር
  • የተሽከርካሪ ብድር
  • የግንባታ ማሽነሪ ብድር
  • ከፊል የፋይናንስ ድጋፍ
  • የተውጣጣ ብድር
  • ለእርሻ የሚውሉ የጊዜ ገደብ ብድሮች
  • የፈጠራ ሐሳብ የፋይናንስ ድጋፍ

የመንቀሳቀሻ ካፒታል

'

  • የኦቨርድራፍት አቅርቦት
  • ከተፈቀደው መጠን በላይ ገንዘብ ወጪ ማድረግ
  • በሸቀጥ መያዥያነት የሚሰጥ ብድር አቅርቦት
  • የገቢ እቃዎች የብድር ደብዳቤ አቅርቦት
  • ቅድመ ጭነት የወጭ ንግድ ብድር አቅርቦት
  • ተዘዋዋሪ የወጭ ንግድ ብድር አቅርቦት
  • የወጭ ንግድ ቢል የቅድመ ክፍያ አቅርቦት
  • የዋስትና ደብዳቤ አቅርቦት
  • የገቢ ንግድ የብድር ደብዳቤ ማወራረጃ ብድር

ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጥ አገልግሎት

አነስተኛ የፋይናንስ አገልግሎት ተቋማት የሚባሉት አነስተኛ ገቢ ላላቸው (ወይም ድሃ ለሆኑ) የኅብረተሰብ ክፍሎች የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ናቸው። ለአነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጡ ብድሮች፡-

  • ተቋማቱ ከአጭር እስከ መካከለኛ ጊዜ ውስጥ እንዲመልሷቸው የሚሰጧቸው የብድር ዓይነቶች ናቸው፤
  • ተቋማቱ የሚያጋጥማቸውን የፋይናንስ ዕጥረት ለመቅረፍ ብድር በመስጠት የተቋማቱን የማበደር አቅም አጎልብተው እነዚህ ተቋማት ለአነስተኛ የሥራ ፈጣሪዎች በቀላሉ ብድር እንዲያቀርቡ ይረዳሉ፤
  • በድርድር በተመሠረተ የወለድ ምጣኔ ሊቀርቡ ይችላሉ

ሌሎች የብድር ዓይነቶች

'

  • የባንክ ለባንክ ብድር
  • የብድር ግዢ
  • ከተፈቀደው በላይ ወጪ ማድረግ
  • የድርጅት ቦንድ ብድር
  • በሸቀጥ መያዣነት የሚሰጥ ብድር