አቶ አቤ በፓናል ውይይቱ ላይ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተለይ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉን እንዲሁም ከፍተኛ ብድር በተመጣኝ የወለድ ምጣኔ ለረጅም ጊዜ ብድር ከ16.5 ፐርሰንት በማይበልጥ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ባንኩ እያቀረበ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል።
በየቀኑ በርካታ የሳይበር ጥቃቶች ባንኩ ላይ እንደሚሞከሩ የገለፁት አቶ አቤ፣ በባንኩ የተዘረጋው ሲስተም በአግባቡ የሚከላከል እና ሥርዓቱን ሰብሮ ለመግባት የሚፈልግ የትኛውም አጥቂ አልፎ መሔድ የማይችለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሲቢኢ በጄ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት በዲጂታል አማራጭ ለደንበኞች ብድር ለማቅረብ የተዘጋጀ አገልግሎት መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆልሴል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ቦኩ ቤኛ ተናግረዋል።