የተቀማጭ ሒሳብ ዓይነቶች

1. ኢ.ን.ባ የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ እና በሕጋዊነት ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች (ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ማኀበራት) የሚሰጣቸው ወለድ የሚከፈልባቸው የሒሳብ ዓይነቶች ናቸው፤ 2. ቢያንስ በ7% ምጣኔ ወለድ በየዓመቱ የሚታሰብ እና በየእለቱ የሚሰላ ወለድ ያስገኛሉ። 3. ባለሒሳቦች ለድንገተኛ ወጪ፣ ዕድሜ ሲገፋ ለሚያስፈልግ ወጪ፣ የተወሰኑ ፍላጎቶቸን ለማሟላት፣ ለወደፊት ኢንቨስትመንት፣ ከድንገተኛ የእሳት አደጋ እና ስርቆት ለመዳን የሚያስችላቸውን ገንዘብ ለመቆጠብ ያስችሏቸዋል፤

የተቀማጭ ሒሳብ ዓይነቶች

የቁጠባ ሒሳብ ዓይነቶች

  • መደበኛ የቁጠባ ሒሳብ
  • የሴቶች የቁጠባ ሒሳብ
  • የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ
  • የወጣቶች የቁጠባ ሒሳብ
  • የትምህርት የቁጠባ ሒሳብ
ተንቀሳቃሽ ሒሳብ

ተንቀሳቃሽ ሒሳብ

ተንቀሳቃሽ ሒሳብ ወለድ የማየከፈልበት የሒሳብ ዓይነት ሆኖ የባንኩን መስፈርት ለሚያሟሉ እና በሕጋዊነት ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች (ግለሰቦች፣ ድርጅቶች፣ ማኀበራት) በስማቸው የሚከፈት ሒሳብ ሲሆን የሚንቀሳቀሰው ማንበብ እና መጻፍ በሚችሉ ግለሰቦች ብቻ ነው፡፡ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ ለመክፈት ዝቅተኛው ተቀማጭ የብር መጠን ለግለሰቦች 500 ብር ሲሆን ለድርጅቶች እና ማኀበራት 1000 ብር ነው፡፡

  • መደበኛ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ
  • ልዩ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ
  • የኢሲኤክስ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ
ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚከፈት ተንቀሳቃሽ ሒሳብ

ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚከፈት ተንቀሳቃሽ ሒሳብ

ይህ ተንቀሳቃሽ ሒሳብ ነዋሪነታቸው ከሀገር ውጪ ለሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች እንዲሁም ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚከፈት ሒሳብ ሲሆን አገልግሎቱም ለሀገር ውስጥ ክፍያዎችን ለመፈጸም የሚውል ነው፡፡ የዚህ ዓይነት ሒሳብ ወለድ የማየከፈልበት የሒሳብ ዓይነት ሆኖ ነገር ግን በውስን የጊዜ ገደብ ለሚቀመጡ የዳያስፖራ ሒሳቦች እና ተመላሽ ላልሆኑ ዳያስፖራ ሒሳብ ለከፈቱ ደንበኞች ወለድ ይከፈላቸዋል፡፡ ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚከፈት ተንቀሳቃሽ ሒሳብ በተመረጡ የባንኩ ቅርንጫፎች የሚሰጥ የአገልግሎት ዓይነት ነው፡፡

  • ኢምባሲዎች
  • ዲፕሎማቶች
  • የውጭ ባለሀብቶች
  • የአለም አቀፍ ድርጅቶችና ሰራተኞች
  • ከሀገር ውጭ ተመላሽ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
  • ለወጪ ንግድ