መንግስት የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ተወዳዳሪ እና ሳቢ ለማድረግ ገበያ መር የሆኑ ፖሊሲዎችን እና እስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። ይህንንም ተከትሎ በባንክ ስራ ዘርፍ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ ሲሆን፤ የባንክ ኢንዱስትሪውም በአቅርቦት እና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የዋጋ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በገበያው ውስጥ ጠንካራ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲዘልቅና በሀገራችን የኢኮኖሚ ግንባታ ላይ ያለውን የጎላ ድርሻ አጎልብቶ መዝለቅ ይችል ዘንድ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ቀልጣፋ ለማድረግ በርካታ የትራንስፎርሜሽን ስራዎችን እያከናወነ ከመሆኑም በተጨማሪ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ አዳዲስ አማራጭ የብድር አገልግሎቶችን ለማስጀመር በሂደት ላይ ይገኛል። ይሁንና ባንካችን እየተገበረው ያለው ሪፎርም አጠቃላይ የኦፕሬሽንና የአስተዳደር ወጪ እድገትን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ያስቻለው ቢሆንም በተለያየ ምክንያት እየተከሰተ ያለው አጠቃላይ የቁጠባ ማሰባሰቢያ ወጪ ከፍተኛ መሆንና ባንካችን ለሚሰጠው የብድር አገልግሎት የሚያስከፍለው የወለድ ምጣኔ በገበያ ላይ ከሚታየው የወለድ ምጣኔ አንጻር ሲታይ በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ በባንካችን ዘላቂ ትርፋማነት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ፈጥሯል። ስለሆነም ይህንን ለማስተካከልና ባንካችንን በፋይናንስ ዘርፉ የሚገባውን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል ለሚሰጠው የብድር አገልግሎት ወጪውን ታሳቢ ያደረገ መጠነኛ የብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ነገር ግን የግብርና ዘርፍን ከማበረታታት አንፃር የወለድ ምጣኔው የተቀነሰ ሲሆን፤ የሕብረተሰቡን የመክፈል አቅም ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለኮንዶሚኒየም መኖሪያ ቤቶች ብድር የሚከፈለው የወለድ መጠን ባለበት እንዲቀጥል ተወሰኗል። በመንግስትና በግል ድርጅት ተበዳሪዎች መካከል የነበረው የምጣኔ ልዩነትም ተስተካክሏል፡፡ በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ. ከማርች 7 ቀን 2025 ጀምሮ ባንካችን የዋጋ ማሻሻያውን ተግባራዊ እንደሚያደርግ እያስታወቅን የተደረገው የዋጋ ማሻሻያ ዝርዝር ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተመላክቷል። https://combanketh.et/cbeapi/uploads/Lending_Rate_Change_be8c8d4bfc.pdf
ትላንት ለገንዘብዎ ሁነኛ ባላደራ ሲፈልጉ በመላው ሀገራችን ቅርንጫፎቹን በመክፈት እርስዎ ወዳሉበት የደረሰው ባንካችን፣ ዛሬም በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ባለችው ዓለማችን፤ ከዘመኑ ጋር እየዘመነ አማራጮችዎን እያሰፋና ፍላጎትዎን እያሟላ በተለመደው ትጋቱ ቀጥሏል! ትጋት እና ጥረታችን ግብ መምታት ስኬቱ የሚለካው በርስዎ እርካታና ደስታ ነውና ለዚህ እውነት ቃላችንን ልናድስ "የላቀ አገልግሎት ደስተኛ ደንበኛ" በሚል መሪ ቃል የደንበኞች አገልግሎት ወርን እናከብራለን፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዘመናት በአብሮነት ለዘለቃችሁ ክቡራን ደንበኞቹ ምስጋናውን እያቀረበ ከታህሳስ 24 እስከ ጥር 25 የሚከበረው የደንበኞች አገልግሎት ወር የናንተ ነውና አብራችሁን እንድትሆኑ በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን። ከዚሁ ክብረ በዓል ጋር ተያይዞ የተዘጋጀውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የጉዞ ሂደት የሚያሳይ አውደ-ርዕይ እና አዲሱን የዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ከታህሳስ 24 እስከ ታህሳስ 30 በዋና መሥሪያ ቤታችን ተገኝተው እንዲጎበኙ ተጋብዘዋል።
ምዝገባው ታህሳስ 15 / December 24, 2024/ ይጠናቀቃል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስያሜ ስፖንሰር የሆነበት ነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር በየዙሩ 1.8 ሚልዮን ብር እንዲሁም ለአሸናፊዎች አሸናፊ 5 ሚሊዮን ብር ሽልማት፤ ምርጥ አምስት ዉስጥ ለሚገቡ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዣ የብድር እድል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያገኙበት የምእራፍ አራት ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሁለት ሳምንት ብቻ ይቀራል፡፡ የሥራ ሀሳብዎን ወደ ነጋድራስ በማምጣትዎ ስራዎን ያስተዋዉቃሉ፤ ከአንጋፋ ዳኞች ጠቃሚ ምክር ያገኛሉ ፤ ያለማስያዣ የብድር ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡ ለመመዝገብ ሊንኩን (https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx) ይጠቀሙ፡፡ ይመዝገቡ ፤ ይወዳደሩ፤ ይሸለሙ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የነጋድራስ የሥራ ፈጠራ ውድድር የቴሌቪዥን ፕሮግራም የስያሜ ስፖንሰር ነው። ነጋድራስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ፈጠራ ውድድር የምዕራፍ አራት ምዝገባ እየተካሄደ ነው። ነጋድራስ በየምዕራፉ 1.8 ሚሊየን ብር ይሸልማል። ለ አሸናፊዎች አሸናፊ ደግሞ 5 ሚሊዬን ብር ተዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በምርጥ አምስት ውስጥ ለሚካተቱ ተወዳዳሪዎች ደግሞ ያለማስያዥያ የብድር እንዲያገኙ አመቻችቶላቸዋል፡፡ ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ፦ https://ebc.et/NegadrasRegistration.aspx ተመዝገቡ፣ ተወዳደሩ፣ አሸንፉ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከተሉትን የግል መረጃ ደኅንነት ምክሮች እንድትተገብሩ በጥብቅ እናሳስባለን! • የካርድ ባንኪንግ አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ በሚያደርጉት ነገር ላይ ብቻ ያተኩሩ፤ ትኩረትዎን የሚያስተጓጉሉ እንደ ሞባይል ስልክ እና መሰል ነገሮቸን አይጠቀሙ፡፡ • የሚስጢር ቁጥርዎን እየቀየሩ ይያዙ ፤ በሚቀይሩበትም ጊዜ ከማንኛውም የግል መረጃ ለምሳሌ የልደት ቀኖች፣ የስልክ ቁጥሮች ጋር አያገናኙ፡፡ • የተንቀሳቃሽ ስልክዎ ላይ የሚጭኗቸውን መተግበሪያዎች ሲያወርዱ አፕስቶር ፣ ፕሌይስቶርን ብቻ ይጠቀሙ፡፡ • ደኅንነቱ ያልተረጋገጠ ድረ-ገጽ እና የማኅበራ ሚዲያ ገጿችን አይጠቀሙ፡፡ • ግብይትዎን በሚያካሂዱበት ጊዜ ችግር ቢያጋጥሞ ከሚመለከታችው የባንኩ ሠራተኞች ውጪ የማንንም እገዛ አይጠይቁ፡፡ • የኤ.ት.ኤም ማሽን ላይ ሲጠቀሙ የሚስጢር ቁጥሮ እንዳይታይ፤ የኤቲኤም ቁልፍ ሰሌዳውን ሰውነትዎን ተጠቅመው በመሸፈን፤ በቅርብ የቆሙ ሰዎች እንይመለከቱ ይከላከሉ፡፡ • ከግብይት በኋላ ካርዱን መቀበሎን ያረጋግጡ፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስልክ በመደወልም ሆነ በጽሁፍ መልዕክት በመላክ የባንክ አገልግሎት ስለማይሰጥ፤ ከዚህ መሰል መጭበርበሮች እንድትጠነቀቁ ያሳስባል! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
ሲቢ ኑር ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ሲሆን በመደበኛው የባንክ አገልግሎቶች ላይ በፍላጎትም ዪሁን በሀይማኖት ምክንያት አገልግሎቱን ማግኝት ላልቻሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የቀረበ ሁሉን አቀፍ የባን አገልግሎት ነው፡፡ ይህም አገልግሎት የተመሰረተው በሸሪያ የንግድ እንቅስቃሴ ሕግ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/72/2019 መሰረት ነው፡፡
የንግድ አገልግሎቶች
ዲጂታል የባንክ አገልግሎት
አቶ አቤ ይህ ስትራቴጂካዊ ትብብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያለውን ሰፊ የገበያ ድርሻ በመጠቀም፤ በቨርቹዋል የካርድ አገልግሎት የባንኩን ከ40 ሚሊየን በላይ ደንበኞች የዘመናዊ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡
የሲቢኢ ኑር ፕሮዳክት ዴቨሎፕመንት እና ቢዝነስ ኤክስፓንሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ አንዋር መሐመድ ደንበኞች ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ለማበረታታት የሽልማት መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
ባንኩ በረመዷን ፆም ወቅት ድጋፍ ማድረጉ ለማህበረሰቡ ያለውን ቅርበት እንደሚያሳይም ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በበኩላቸው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በመስጠት 11 ስኬታማ ዓመታትን ያስቆጠረው የሲቢኢ ኑር አገልግሎት በደንበኞቹ ዘንድ ተአማኒነት በማትረፉ ውጤታማ ስለሆነ ለአጋርነታችሁ ምስጋና ይገባችሃል ብለዋል፡፡
ባቡል ኽይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በቀን ከአራት ሺህ ስምንት መቶ በላይ አባወራዎችን የምገባ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
በቀን ከ4800 በላይ አባወራዎችን የምገባ አገልግሎት እና ከ18 ሺህ በላይ የቤተሰብ አባላትን በያሉበት የምገባ አገልግሎት ለሚሰጠው ባቡል ኼይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገኘ::
Branchs
Customers
Partners
Transactions per Month