ባንኩ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ማክበር የጀመረውን የደንበኞች የአገልግሎት ወር ምክንያት በማድረግ ከደንበኞች ጋር የሚያደርገውን ውይይት በመቀጠል በዛሬው እለት ከሪቴይል ደንበኞች ጋር ውይይት አድርጓል። በዋናው መ/ቤት የተካሄደውን ውይይት የከፈቱት የባንኩ ከስተመር ኤክስፔሪየንስ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሃይለእየሱስ በቀለ ባንኩ ከደንበኞቹ ጋር በሚያደርገው ውይይት ከደንበኞቹ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችለውን ግብአት እያገኝ ነው ብለዋል። እየተደረጉ ባሉት ውይይቶች በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ይበልጥ ለመረዳት ደንበኞች የሚሰጧቸው አስተያየቶች እንዳገዙ አቶ ሃይለእየሱስ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስረታው አንስቶ በተለይም ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ ያከናወናቸውን የሪፎርም ስራዎች በተመለከተ በባንኩ የሪቴይል ቢዝነስ ዴቨሎፕመንት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ቅዱስ ምንይሹ ገለፃ ተደርጓል። ደንበኞችም በዲጂታል ባንክ አገልግሎት፣ በሲቢኢ ኑር እና አጠቃላይ የባንክ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ አንስተው የባንኩ ሪቴይልና ቅርንጫፍ ባንኪንግ ተቀዳሚ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ደረጀ ፉፋና በሚመለከታቸው የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ! https://www.youtube.com/commercialbankofethiopia https://www.tiktok.com/@combankethiopia https://www.facebook.com/share/p/15m4WM7pgH/